Artist
አንቺ ሰው ልገልጽሽ ቃላት አጣውልሽ፤
ጠፋና የምለው ገና ሳልጀምረው፡፡
ልንገርሽ እማ፤
እንድታውቂው ልሞክር፤
ቃል ልደርድር፤
ከየት ብዬ ልጀምር
(ልጀምር ነይ ነይ)
ልንገርሽ እማ፤
ልገጥምልሽ ሞከርኩና ቤቱን ከየት ልምታው
ያንቺ ፍቅር ቤት አይበቃው
(አይበቃው ሄይ ሄይ)
ልንገርሽ እማ
እችል መስሎኝ እዘርፈው ቃላት ገጣጥሜ
እኔን ብሎ ባለቅኔ
(ድንቄም ባለቅኔ ሄይ ሄይ)
ልንገርሽ እማ
አቅቶኛል ልገልጽሽ
እንኳን ልክስሽ ብቻ ይወድሻል ልጅሽ
አይ ልጅሽ
አይ ልጅሽ
አዝማች
ይወድሻል ልጅሽ እምዬ
ሞትን ባስቀረው ላንቺ ብዬ
እማማዬ እማማዬ
ቃላት ስላጣውልሽ
ሙዚቃዬ ፍቅሬን ይንገርሽ
እማማዬ እማማዬ
እማዬ አዬ
በላይ በላይ ላንቺ
ደስታውን ድርብርብ ያርገው
የሰማዩ ልቡ የታመነው
አሜን
በላይ በላይ ላንቺ
ደስታውን ድርብርብ ያርገው
የሰማዩ ልቡ የታመነው
አሜን
ልንገርሽ እማ
ዛሬ ትልቅ ሰው ተብዬ
ለሰው ልታይ እንጂ
ላንቺ የማላድግ ልጅ
ሁሌም ህፃን ልጅ (ሄይ.. ሄይ..)
ያገባሽው ግስላማ ማን ሰው ይችለዋል
ባንቺ ሲሉት ብቻ ስምሽ ያበርደዋል (ሄይ.. ሄይ..)
ድጋሜ ልፍጠርህ ብሎ ምርጫ ቢያቀርብልኝ
አንቺን እለው ድገምልኝ
አዬ ድገምልኝ (ነይ ነይ)
አድጌአለሁ በእጆችሽ
ሰው ነኝ እና በምክርሽ
ጠብቆኛል ፀሎትሽ
ፍቅሬ አንቺ ነሽ፡፡
አዝማች
ይወድሻል ልጅሽ እምዬ
ሞትን ባስቀረው ላንቺ ብዬ
እማማዬ እማማዬ
ቃላት ስላጣውልሽ
ሙዚቃዬ ፍቅሬን ይንገርሽ
እማማዬ እማማዬ
እማዬ አዬ
አደዬ በላዬ
አናናዬ…